ማህበሩ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጥንካሬውን እንደሚያስቀጥል ተነገረ፡፡

በወላይታ ልማት ማህበር የሚተዳደረው የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በወላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ ሀኖ በአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ሆኖ ውጤታማ ተማሪዎችን እያፈራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በያዝነው 2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቱን ቁጥር በመጨመር በዞኑ ሶስት አካባቢዎች በይፋ ስራ አስጀምሯል፡፡ በዛሬው ዕለት አራተኛው የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በገሱባ ከተማ አስተዳደር በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡ […]

ማህበሩ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጥንካሬውን እንደሚያስቀጥል ተነገረ፡፡ Read More »

ማህበሩ በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ስራ አስጀምሯል።

የወላይታ ልማት ማህበር ላለፉት ጊዜያት በወላይታ ዞን በቁጥር አንድ ብቻ የነበረውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሶስት ትምህርት ቤቶችን ለመከፈት እንቅስቃሴ ጀምሮ ዕቅዱን በማሳካት በያዝነው ሳምንት ሁለተኛውን ትምህርት ቤት በአረካ ከተማ አስተዳደር በይፋ ስራ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በይፋ

ማህበሩ በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ስራ አስጀምሯል። Read More »

በዛሬዉ ዕለት የወላይታ ሊቃ አረካ ትምህርት ቤት በይፋ ስራ ጀምሯል።

በማስጀመሪያዉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያምን ጨምሮ ሌሎች የወላይታ ዞን የስራ ኃላፊዎች፣ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ናና እና የወልማ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። በቀጣይ ቀናትም የቦዲቲና ገሱባ ትምህርት ቤቶች በይፋ ተከፍተዉ ስራ የሚጀምሩ ይሆናል።

በዛሬዉ ዕለት የወላይታ ሊቃ አረካ ትምህርት ቤት በይፋ ስራ ጀምሯል። Read More »

ወላይታ ልማት ማህበር የሚያስተዳድራቸው የሊቃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ አራት ከፍ አለ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ላለፉት 16 ዓመታት በዞኑ ማዕከል ወላይታ ሶዶ አንድ ትምህርት ቤት ከፍቶ ብሩህ አዕምሮ እያላቸው በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ጥራት ያለውን ትምህርት ማግኘት ያልቻሉ ተማሪዎችን ሙሉ ስኮላርሺፕ በመስጠትና ወጪ የሚጋሩ ተማሪዎችን በመቀበል ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠት ከወላይታ ዞን አልፎ በደቡብ ክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የህክምና ዶክተሮችን፣ መሀንዲሶችንና በሌሎች ሙያ የተሰማሩ ባለሙያዎችን አፍርቷል፤

ወላይታ ልማት ማህበር የሚያስተዳድራቸው የሊቃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ አራት ከፍ አለ፡፡ Read More »

የዳግም ትምህርት ዕድል ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከሉሚኖስ ፈንድ (Luminos Fund) በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች በ2017 የትምህርት ዘመን የሚተገብረውን የዳግም ትምህርት ዕድል (Second Chance Education) ፕሮጀክት የወረዳዎቹ ትምህርት አመራሮች በተገኙበት አስተዋወውቋል፡፡ ማህበሩ ፕሮጀክቱን በ2017 የትምህርት ዘመን በዳሞት ጋሌ፣ ቦሎሶ ሶሬ እና ባይራ ኮይሻ ወረዳዎች ይተገብራል፡፡ በዛሬው ዕለት ከወረዳዎቹ ለተወጣጡ የትምህርት አመራሮች ስለፕሮጀክቱ አተገባበር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ

የዳግም ትምህርት ዕድል ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡ Read More »

GreenLegacy የማህበሩ ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡ ወላይታ ልማት ማህበር መንግስት ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት የራሱን ድርሻ ሲወጣ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ

GreenLegacy የማህበሩ ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡ Read More »

ማህበሩ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች የቤት ኪዳን ቆርቆሮ እና ሚስማር ድጋፍ አበረከተ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ከተቋቋመለት ዋንኛው ዓላማ አንዱ የበጎ አድራጎት ስራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከምስረታውም ጀምሮ በበጎ ስራ የሚታወቀው ይህ ማህበር መንግስት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ በዛሬው ዕለት በኪንዶ ኮይሻ እና ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳዎች ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ለቤት መስሪያ የሚሆን የቤት ኪዳን ቆርቆሮ እና ሚስማር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ለወረዳዎቹ አመራሮችና አቅመ ደካማ ቤተሰቦች በስፍራው

ማህበሩ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች የቤት ኪዳን ቆርቆሮ እና ሚስማር ድጋፍ አበረከተ፡፡ Read More »

ለተፋጠነ ትምህርት መርሀ ግብር አመቻች መምህራን እና መርሀ ግብሩን ለተገበሩ ወረዳዎች ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡

ለተፋጠነ ትምህርት መርሀ ግብር አመቻች መምህራን እና መርሀ ግብሩን ለተገበሩ ወረዳዎች ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡ የወላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ Luminos Second Chance Education ፕሮጀክት ነው፡፡ ልማት ማህበሩ በዚሁ ፕሮጀክት በሶስት በባይራ ኮይሻ፣ ዳሞት ጋሌና ቦሎሶ ሶሬ ወረዳዎች ከሉሚኖስ ፈንድ ኢትዮጵያ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ እድሜያቸው ከ9-14

ለተፋጠነ ትምህርት መርሀ ግብር አመቻች መምህራን እና መርሀ ግብሩን ለተገበሩ ወረዳዎች ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡ Read More »

የኩባንያው የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም በከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኩባንያው የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም በከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ለወላይታ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ገንብቶ ያጠናቀቀውን ቢሮ ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡ በወላይታ ልማት ማህበር የሚተዳደረው የዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ጥራት ያላቸውን ግንባታዎች በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት ገንብቶ እንደሚያጠናቅቅ ይታወቃል፡፡ ኩባንያው ከግንባታ ስራዎች በተጨማሪ ማሽኔሪዎችን በማከራየትና ሲሚንቶ በማከፋፈል ለህብረተሰቡ አገልግሎት

የኩባንያው የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም በከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ Read More »

ማህበሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ የፌዴራልና ክልል ተቋማት እንዲሁም የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጋር በልማት ዙሪያ ዉይይት አካሄደ።

ማህበሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ የፌዴራልና ክልል ተቋማት እንዲሁም የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጋር በልማት ዙሪያ ዉይይት አካሄደ። በዉይይት መድረኩ ልማት ማህበሩ የአባላትን ቁጥር በማሳደግና የገቢ ማስገኛ ተቋማትን በማጠናከር ከለጋሾች ድጋፍ በመላቀቅ በራሱ እግር መቆም እንዳለበት በአጽንኦት አስተያየት ተሰጥቷል። በተጨማሪም የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑ ተመልክቷል። ዉይይቱን የማህበሩ የበላይ ጠባቂና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

ማህበሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ የፌዴራልና ክልል ተቋማት እንዲሁም የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጋር በልማት ዙሪያ ዉይይት አካሄደ። Read More »