ልማት ማህበሩ ከሳቫና ፕሪንቲንግ ጋር በመተባበር ለአራት ትምህርት ቤቶች ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ።

ወላይታ ልማት ማህበር የልማት ስራዎችን ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ይሰራል። ማህበሩ በሰዉ ሀብት ልማት በአጋርነት ከሚሰራቸው ተቋማት አንዱ ሳቫና ፕሪንቲንግ ሲሆን ለዘንድሮ የትምህርት ዘመን በወላይታ ዞንና ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የደብተር፣ እስክሪብቶ እና ሞንቴሶሪ ዕቃዎችን ያካተተ እንዲሁም በገንዘብ ሲተመን ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነዉ። […]

ልማት ማህበሩ ከሳቫና ፕሪንቲንግ ጋር በመተባበር ለአራት ትምህርት ቤቶች ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ። Read More »

በመትከል ማንሰራራት

የማህበሩ ሰራተኞች በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡ ወላይታ ልማት ማህበር በአገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት የሚካሄደውን ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በማህበሩ የኮካቴ እንስሳት እርባታ ማዕከል ቅጥር ግቢ አካሂደዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና

በመትከል ማንሰራራት Read More »

ማህበሩ ከየትኛዉም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ ተነገረ።

በወላይታ ልማት የጠበላ ከተማ ቅርንጫፍ አባላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት ተካሂዷል ።በጉባኤው የከተማዉ የልማት ማህበሩ አባላት የተገኙ ሲሆን የማህበሩና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2024 እ.አ.አ ክንዉን ሪፖርትና የ2025 ዕቅድ በዝርዝር ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዉ ጸድቀዋል።ጉባኤዉን በንግግር የከፈቱት የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እጩ ዶ/ር ታረቀኝ ገቼረ ማህበሩ በአሁን ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ ይሻል በማለት ማህበሩን ማጠናከር

ማህበሩ ከየትኛዉም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ ተነገረ። Read More »

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአረካ ከተማ የሚገኝውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጎበኙ!።

በወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጉብኝታቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረዉ እንዲማሩ ምክር ሰጥተዋል። ለትምህርት ቤቱ ውጤታማነት ሁሉም ባለ ድርሻ አካለት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸዉ አሳስበዎል በጉብኝቱ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያምን ጨምሮ የዞኑና የአረካ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአረካ ከተማ የሚገኝውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጎበኙ!። Read More »

ከጎዳና ለተመለሱ ልጆች ወላጆች የንግድ ስራ መነሻ ካፒታልና ንብረት ተሰጣቸው፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር አሜሪካን ሀገር ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማና አካባቢው ከሚገኙ የወላይታ ተወላጆች ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በመምጣት ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትን ወደቤተሰቦቻቸው በመመለስ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ እነዚህን ህጻናት በማቋቋምና በዘላቂነት የልጆቹን ቤተሰብ ኑሮ ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ የሚታወስ ሲሆን ለልጆቹ የትምርት ቁሳቁስ፣ ቀለብ፣ የጤና መድህን ሽፋንና ሌሎች

ከጎዳና ለተመለሱ ልጆች ወላጆች የንግድ ስራ መነሻ ካፒታልና ንብረት ተሰጣቸው፡፡ Read More »

“ልማት ማህበሩ ለዞኑ ሁለንተናዊ ብልጽግና አስተዋጽኦ ያላቸው በርካታ አኩሪ ተግባራት አከናውኗል።”አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም

የወላይታ ልማት ማህበር (ወልማ) 24ኛ ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የማህበሩ የበላይ ጠባቂ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም የወላይታ ልማት ማህበር ባለፉት 24 ዓመታት በግብርና በሥራ ዕድል ፈጠራ በጤና በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በመሠረተ ልማት ሥራዎች ለዞኑ ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ያላቸው በርካታ ተግባራት ተፈጽመዋል ብለዋል። የህዝባችን ፍሬ የሆነው

“ልማት ማህበሩ ለዞኑ ሁለንተናዊ ብልጽግና አስተዋጽኦ ያላቸው በርካታ አኩሪ ተግባራት አከናውኗል።”አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም Read More »

ጠቅላላ ጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።

ጠቅላላ ጉባኤው የወላይታ ልማት ማህበርን የሚመሩ ቦርድ አመራሮች ምርጫ በማካሄድ ተጠናቅቋል። ጠቅላላ ጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን ሰብሳቢውም ለጉባኤው የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል። የልማት ማህበሩን የሚመሩ የአመራር ቦርድ አባላት:- 1. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገ/መስቀል ጫላ የወላይታ ልማት ማህበር የቦርድ

ጠቅላላ ጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል። Read More »

ማህበሩ ለ10 ትምህርት ቤቶች 310 ኮምፒውተሮችንና 10 ሰርቨሮችን አበረከተ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በዞኑ ውስጥ የተለያዩ የልማት ተግባራትን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ መንግስት የያዛቸውን የልማት ግቦች በትብብር ለማሳካት የራሱን ድርሻ እያበረከተ ቆይቷል፤ እያበረከተም ነው፡፡ ማህበሩ መንግስት በትምርትና ስልጠና ያየዘውንና የሰለጠና፣ ሀገር የሚያቀናና ስራ ፈጣሪ ዜጋ ለማፍራት የያዘውን ትልም ለማሳካት በራሱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚያደርገው ጥረት በዛሬው ዕለት ET- LEARNS ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያገኘውን

ማህበሩ ለ10 ትምህርት ቤቶች 310 ኮምፒውተሮችንና 10 ሰርቨሮችን አበረከተ፡፡ Read More »

ማህበሩ ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ 8 የመማሪያ ክፍሎች የያዘ 2 ብሎክ ህንጻ አስመረቀ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት የትኩረት አቅጣጫ ዘርፍ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ከመንግስት ጎን በመሆን ለትምህርት ተደራሽነትና ጥራት መረጋገጥ የራሱን ሚና ተወጥቷል፤ እየተወጣም ነው፡፡ ማህበሩ ከዚህ በፊት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የመማሪያ ህንጻዎችን በመገንባት ለመንግስት ያስረከበ ሲሆን በዘሬው ዕለት በኦፋ ወረዳ ሙሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለት ብሎክ 8 የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ህንጻ ገንብቶ በማጠናቀቅ

ማህበሩ ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ 8 የመማሪያ ክፍሎች የያዘ 2 ብሎክ ህንጻ አስመረቀ፡፡ Read More »

ማህበሩ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮምፒውተርና ሰርቨር ድጋፍ አገኘ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በትብብር ከሚሰራቸው ተቋማት አንዱ የሆነውና ከዚህ በፊት ከማህበሩ ጋር በመሆን በዞኑ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርትን ለማስፋፋት የራሱን ድርሻ እያበበረከተ የቆየ ET-LEARNS የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ኮምፒውተሮችና ሰርቨር ለልማት ማህበሩ አበርክቷል፡፡ ድጋፉ 310 ክሮም ቡክ

ማህበሩ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮምፒውተርና ሰርቨር ድጋፍ አገኘ፡፡ Read More »