በዛሬው ዕለት የወላይታ ሊቀ ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑ 31 የህክምና ዶክተሮች ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ከድህነትና ኋላ ቀሪነት የተላቀቀ ወላይታን የማዬት ራዕዩን እውን ለማድረግ ትምህርት ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን በማመን በኢትዮጵያ ሚሊኒዬም ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን አቋቋመ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በስኬት ጎዳና በመጓዝ ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፍራት አካባቢውን በበጎ ጎን ስሙ ከፍ እንዲል የራሱን ሚና ሲጫወት ቆይቷል፡፡ ትምህርት ቤቱ ከ2005 ዓ.ም […]

በዛሬው ዕለት የወላይታ ሊቀ ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑ 31 የህክምና ዶክተሮች ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡ Read More »

ማህበሩ በወላይታ ሊቃ ት/ቤት ባለአንድ ብሎክ የመማሪያ ህንጻ ግንባታ አስጀመረ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በሀገር አንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስመጥር እና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፋራት የሚታወቀውን ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ለማጠናከርና ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ ባሳለፍነው ዓመት የሀብት ማሰባበሰቢያ መርሀ ግብር በመንደፍ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ ሀብት ማሰባበሰቡ ይተወቃል፡፡ ለትምህርት ቤቱ ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ድጋፍ ለማድረግ በወቅቱ ቃል ከገቡ ባለሀብቶች መካከል ሀጂ ሙስጠፋ አወል (የሙለጌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለቤት) እና ቤተሰቡ አንዱ

ማህበሩ በወላይታ ሊቃ ት/ቤት ባለአንድ ብሎክ የመማሪያ ህንጻ ግንባታ አስጀመረ፡፡ Read More »

በ9 ወራት ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ሀብት በመሰብሰብ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ከድህነትና ኋላቀርነት የተላቀቀ ወላይታን የማየት ትልሙን ለማሳካት በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች የልማት ተግባራትን እያከናወነ ነው፡፡ ማህበሩ በ2024 እ.አ.አ በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያና በተቀናጀ ጤና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ በመነሳት ላለፉት 9 ወራት የልማት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በግምገማው ማህበሩ በዓመቱ በ9 ወራት ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ሀብት በመሰብሰብ የልማት

በ9 ወራት ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ሀብት በመሰብሰብ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ Read More »

ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ልጆች የአልባሳትና ጫማ ድጋፍ ተበረከተ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በድህነትና በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ወደ ጎዳና የወጡ ልጆችን ከጎዳና ላይ በማንሳት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲቀላቀሉ በማድረግና የቤተሰቦቻቸው ኑሮ በዘላቂነት እንዲሻሻል ከአጋሮች ጋር በመሆን እየሰራ ነው፡፡ ማህበሩ በአገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማና አካባቢው ከሚገኙ የወላይታ ዳያስፖራ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚተገብረው በዚሁ REST (Reintegration and Empowerment of Street Children) ፕሮጀክት ባሳለፍነው ዓመት ልጆችን

ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ልጆች የአልባሳትና ጫማ ድጋፍ ተበረከተ፡፡ Read More »

ማህበሩ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጥንካሬውን እንደሚያስቀጥል ተነገረ፡፡

በወላይታ ልማት ማህበር የሚተዳደረው የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በወላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ ሀኖ በአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ሆኖ ውጤታማ ተማሪዎችን እያፈራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በያዝነው 2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቱን ቁጥር በመጨመር በዞኑ ሶስት አካባቢዎች በይፋ ስራ አስጀምሯል፡፡ በዛሬው ዕለት አራተኛው የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በገሱባ ከተማ አስተዳደር በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ማህበሩ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ጥንካሬውን እንደሚያስቀጥል ተነገረ፡፡ Read More »

ማህበሩ በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ስራ አስጀምሯል።

የወላይታ ልማት ማህበር ላለፉት ጊዜያት በወላይታ ዞን በቁጥር አንድ ብቻ የነበረውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሶስት ትምህርት ቤቶችን ለመከፈት እንቅስቃሴ ጀምሮ ዕቅዱን በማሳካት በያዝነው ሳምንት ሁለተኛውን ትምህርት ቤት በአረካ ከተማ አስተዳደር በይፋ ስራ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በይፋ

ማህበሩ በዞኑ ሶስተኛውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ስራ አስጀምሯል። Read More »

በዛሬዉ ዕለት የወላይታ ሊቃ አረካ ትምህርት ቤት በይፋ ስራ ጀምሯል።

በማስጀመሪያዉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያምን ጨምሮ ሌሎች የወላይታ ዞን የስራ ኃላፊዎች፣ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ናና እና የወልማ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። በቀጣይ ቀናትም የቦዲቲና ገሱባ ትምህርት ቤቶች በይፋ ተከፍተዉ ስራ የሚጀምሩ ይሆናል።

በዛሬዉ ዕለት የወላይታ ሊቃ አረካ ትምህርት ቤት በይፋ ስራ ጀምሯል። Read More »

ወላይታ ልማት ማህበር የሚያስተዳድራቸው የሊቃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ አራት ከፍ አለ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ላለፉት 16 ዓመታት በዞኑ ማዕከል ወላይታ ሶዶ አንድ ትምህርት ቤት ከፍቶ ብሩህ አዕምሮ እያላቸው በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ጥራት ያለውን ትምህርት ማግኘት ያልቻሉ ተማሪዎችን ሙሉ ስኮላርሺፕ በመስጠትና ወጪ የሚጋሩ ተማሪዎችን በመቀበል ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠት ከወላይታ ዞን አልፎ በደቡብ ክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ የህክምና ዶክተሮችን፣ መሀንዲሶችንና በሌሎች ሙያ የተሰማሩ ባለሙያዎችን አፍርቷል፤

ወላይታ ልማት ማህበር የሚያስተዳድራቸው የሊቃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ አራት ከፍ አለ፡፡ Read More »

የዳግም ትምህርት ዕድል ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከሉሚኖስ ፈንድ (Luminos Fund) በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች በ2017 የትምህርት ዘመን የሚተገብረውን የዳግም ትምህርት ዕድል (Second Chance Education) ፕሮጀክት የወረዳዎቹ ትምህርት አመራሮች በተገኙበት አስተዋወውቋል፡፡ ማህበሩ ፕሮጀክቱን በ2017 የትምህርት ዘመን በዳሞት ጋሌ፣ ቦሎሶ ሶሬ እና ባይራ ኮይሻ ወረዳዎች ይተገብራል፡፡ በዛሬው ዕለት ከወረዳዎቹ ለተወጣጡ የትምህርት አመራሮች ስለፕሮጀክቱ አተገባበር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ

የዳግም ትምህርት ዕድል ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡ Read More »

GreenLegacy የማህበሩ ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡ ወላይታ ልማት ማህበር መንግስት ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት የራሱን ድርሻ ሲወጣ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ

GreenLegacy የማህበሩ ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡ Read More »