ልማት ማህበሩ ከሳቫና ፕሪንቲንግ ጋር በመተባበር ለአራት ትምህርት ቤቶች ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ።
ወላይታ ልማት ማህበር የልማት ስራዎችን ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ይሰራል። ማህበሩ በሰዉ ሀብት ልማት በአጋርነት ከሚሰራቸው ተቋማት አንዱ ሳቫና ፕሪንቲንግ ሲሆን ለዘንድሮ የትምህርት ዘመን በወላይታ ዞንና ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የደብተር፣ እስክሪብቶ እና ሞንቴሶሪ ዕቃዎችን ያካተተ እንዲሁም በገንዘብ ሲተመን ከ1.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነዉ። […]











