የወላይታ ልማት ማህበር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የልማት ተግባራትን እንደሚያከናውን ይታወቃል፡፡
ማህበሩ የልማት ስራዎችን በአጋርነት ለመስራት ከ BRTE (Building Resilence Through Education) ፕሮጀክት ጋር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከፕሮጀክቱ የተወጣጣ ቡድን በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ተገኝቶ ልማት ማህበሩን በመጎብኘት የሚሰራቸው ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከልማት ማህበሩ ጋር በዘርፈ ብዙ ተግባራት በትብብር እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡