በፕሮጀክቱ ድጋፍ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል

የወላይታ ልማት ከCBM ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚተገብረው DIDRR (Disability Inclusive Disaster Risk Reduction) ፕሮጀክት አማካይነት በዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ወይዴ እና ዳሞት ሶሬ ወረዳዎች አካል ጉዳተኞችን፣ የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦችንና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማህበር በማደራጀት ገንዘብ በማስቆጠብና ከፕሮጀክቱ የመነሻ ገንዘብ በመጨመር ከየማህበራቱ ብድር እንዲያኙ በማድረግ የንግድ ስራ ዕቅድ አውጥተው እንስሳትን እንድያረቡና በጥቃቅን ንግድ እንዲሰማሩ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
በሶስቱም ወረዳዎች የሚገኙ ማህበራት ለአባላቱ በሰጡት ብድር አባላቱ በእንስስት እርባታና በጥቃቅን የንግድ ስራ ተጠቃሚ ሆነው ኑሮአቸውን እያሻሻሉ እንደሆነ ሰሞኑን ከልማት ማህበሩ የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ምልከታ አድርጓል፡፡
በመስክ ምልከታ ወቅት በማህበር የተደራጁና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ በዳሞት ጋሌ ሀርቶ ቆንጦላ እና ሀርቶ ቡርቅቶ እና በዳሞት ወይዴ ኮዮ ሳኬና ሙንዳጃ ሳኬ ቀበሌያት በበግ፣ በፍየል፣ በወይፈንና ግደር እርባታ እንዲሁም በጥቃቅን ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚና ውጤታማ መሆናቸውን የባለሙያዎች ቡድን ተመልክቷል፡፡
የወላይታ ልማት ማህበር ባሳለፍነው ዓመት ከላይ በተጠቀሱት እና ኪንዶ ኮይሻና ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎች ለሚገኙ ማህበራት ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ብድር እንዲያገኙ ማድረጉን ማስነበባችን ይታወሳል፡: