የወላይታ ልማት ማህበር ከCBM (Christian Blind Mission) ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚያከናወነው አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የአደጋ ስጋት ቅነሳ (Disability Inclusive Disaster Risk Reduction) ፕሮጀከት በዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ እና ዳሞት ወይዴ እንደደሚከናወን ይታወቃል፡፡
ከፕሮጀክቱ ተግባራት አንዱ ለአካል ጉዳተኛ ማህበራት፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳና የማህበረሰብ አካትቶ ልማት ኮሚቴዎች ስለአካል ጉዳተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች፣ ስለአዳጋ ስጋት ቅነሳ እና ስለአካትቶ ልማት ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማመቻት አንዱ ሲሆን ከ19- 21/09/24 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቻው ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሰሶሬ እና ዳሞት ወይዴ ወረዳዎች በነዚህ ርዕሶች ለማህበራቱ አመራሮችና ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሰፊ የሆነ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቿል፡፡
የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ልማት ማህበሩ እየተገበረ ያለው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላቱ በራሳቸው ማህበራቱንና ኮሚቴዎቹን በዘላቂነት መምራትና የየዕለት ተግባራቱን ተከታትለው አካል ጉዳተኞችን በማካተት እና ለአደጋ ስጋት አጋላጭ ሁኔታዎችን መቀነስ እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑን በወላይታ ልማት ማህበር አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የአደጋ ስጋት ቅነሳ (Disability Inclusive Disaster Risk Reduction) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ እንዳለማው ታፈሰ ተናግረዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በወሰዱት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዕውቀት ፕሮጀክቱ በሚያበቃበት ጊዜ ተግባራቱን በራሳቸው እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡