News

WODA News

በዳግም የትምህርት ዕድል ፕሮጀክት አተገባበር እና ዘላቂነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካለት ጋር የምክከር መድረክ ተካሄደ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከሉሚኖስ ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በዳሞት ጋሌ፣ ቦሎሶ ሶሬ እና ባይራ ኮይሻ ወረዳዎች በሚተገብረው “Luminos Second Chance Education” ፕሮጀክት ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ በተለያየ ምክንያት በትምህርት ገበታ የማይገኙ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ በአንድ ዓመት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል አስተምሮ ወደ 4ኛ ክፍል በማዛወር ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር እኩል ያደርጋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዛሬው ዕለት በእስካሁን […]

በዳግም የትምህርት ዕድል ፕሮጀክት አተገባበር እና ዘላቂነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካለት ጋር የምክከር መድረክ ተካሄደ፡፡ Read More »

በወረዳ ደረጃ እየተሰጠ የቆየው የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከCBM (Christian Blind Mission) ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚያከናወነው አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የአደጋ ስጋት ቅነሳ (Disability Inclusive Disaster Risk Reduction) ፕሮጀከት በዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ እና ዳሞት ወይዴ እንደደሚከናወን ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቱ ተግባራት አንዱ ለአካል ጉዳተኛ ማህበራት፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳና የማህበረሰብ አካትቶ ልማት ኮሚቴዎች ስለአካል ጉዳተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች፣ ስለአዳጋ ስጋት ቅነሳ እና ስለአካትቶ

በወረዳ ደረጃ እየተሰጠ የቆየው የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ Read More »

ለማህበሩ ፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች የፋይናንስ ሪፖርት ስልጠና ተሰጠ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከአባላቱ፣ ከረጂ ድርጅቶችና ከገቢ ማስገኛ ተቋማት የሰበሰበውን ሀብት ለታለመለት የልማት ግብ ለማዋል ሀብቱን በዘመናዊ የፋይናንስ አሰራር ይመራል፡፡ ማህበሩ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ የልማት ድርጅት እንደመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የፋይናንስ አሰራሮች ይከተላል፡፡ ይኼም የፋይናንስ አሰራር ስታንዳርድ IFRS/IPSAS (International Financial Reporting Standards/ International Public Sector Accounting Standards) ነው፡፡ ማህበሩ ለፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች

ለማህበሩ ፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች የፋይናንስ ሪፖርት ስልጠና ተሰጠ፡፡ Read More »

በጥቃት ጥበቃ ፖሊሲ ፍሬምወርክና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር በልማት ተግባራቱ ዜጎች እንዲሳተፉ የስራ አካባቢያቸው ለስራ ምቹ እንዲሆን ከአጋር ድርጅቶችና ከመንግስት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ ማህበሩ በራሱ የጥቃት ጥበቃ ፖሊሲ ያለው ሲሆን ባለድርሻ አካላትንም ስለፖሊሲው ለማሳወቅ ስልጠናዎችንና የግንዘቤ ማስጨበጫ መድረኮችን እያመቻቸ አወንታዊ ሚና ሲጫወት ቆይቷል፡፡ ማህበሩ በዛሬው ዕለት ስለጥቃት ጥበቃ ፖሊሲ ፍሬምወርክና አካል ጉዳተኞችን ስለማካተት ከዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ጋሌ እና ዳሞት ወይዴ

በጥቃት ጥበቃ ፖሊሲ ፍሬምወርክና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ Read More »

ከአጋር ድርጅቱ የተወጣጣ ቡድን ልማት ማህበሩን ጎበኘ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የልማት ተግባራትን እንደሚያከናውን ይታወቃል፡፡ ማህበሩ የልማት ስራዎችን በአጋርነት ለመስራት ከ BRTE (Building Resilence Through Education) ፕሮጀክት ጋር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከፕሮጀክቱ የተወጣጣ ቡድን በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ተገኝቶ ልማት ማህበሩን በመጎብኘት የሚሰራቸው ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከልማት ማህበሩ ጋር በዘርፈ

ከአጋር ድርጅቱ የተወጣጣ ቡድን ልማት ማህበሩን ጎበኘ፡፡ Read More »

በፕሮጀክቱ ድጋፍ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል

የወላይታ ልማት ከCBM ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚተገብረው DIDRR (Disability Inclusive Disaster Risk Reduction) ፕሮጀክት አማካይነት በዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ወይዴ እና ዳሞት ሶሬ ወረዳዎች አካል ጉዳተኞችን፣ የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦችንና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማህበር በማደራጀት ገንዘብ በማስቆጠብና ከፕሮጀክቱ የመነሻ ገንዘብ በመጨመር ከየማህበራቱ ብድር እንዲያኙ በማድረግ የንግድ ስራ ዕቅድ አውጥተው እንስሳትን እንድያረቡና በጥቃቅን ንግድ እንዲሰማሩ ማድረጉ

በፕሮጀክቱ ድጋፍ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል Read More »

ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የግብርና ትምህርትና ምርምር ማዕከል ለማቋቋም እየሰራ ነው፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከመንግስት ጋር በመቀናጀት በአkባቢው ልማት በመሰማራት በዞኑ በጎ ለውጦችን በማስመዝገብ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ ትኩረት አድርጎ በሚንቀሳቀስባቸው በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ እና በተቀናጀ ጤና አጋር ድርጅቶች በትብብር የሚሰሩ ሲሆን በዚህም ከበርካታ ተቋማት ጋር በመስራት የካበተ ልምድ አለው፡፡ ማህbሩ በዛሬው ዕለት “Building Resilience through Education (BRTE2)” ከተሰኘ ፕሮጀክት ጋር በወላይታ ዞን የግብርና ትምህርትና

ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የግብርና ትምህርትና ምርምር ማዕከል ለማቋቋም እየሰራ ነው፡፡ Read More »

የወተት ምገባ ተግባር ተጠናከሮ በመቀጠል በሶዶ ከተማ አስተዳደር በሆህተ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅድመ መደበኛ ክፍሎች ተጀምሯል፡፡

የወተት ምገባ ተግባር ተጠናከሮ በመቀጠል በሶዶ ከተማ አስተዳደር በሆህተ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅድመ መደበኛ ክፍሎች ተጀምሯል፡፡ የወላይታ ልማት ማህበር ከ SNV ኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሶዶ ከተማ አስተዳደር በሚተገብረው BRIDGE+ፕሮጀክት ከሚተገብራቸው ተግባራት አንዱ የትምህርት ቤት ወተት ምገባ ነው፡፡ በትምህርት ቤቶች በሚተገበር የወተት ምገባ ለልጆች ዕድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነው ንጽህናው የተጠበቀ ወተት ለቅድመ

የወተት ምገባ ተግባር ተጠናከሮ በመቀጠል በሶዶ ከተማ አስተዳደር በሆህተ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅድመ መደበኛ ክፍሎች ተጀምሯል፡፡ Read More »

ማህበሩ ግብርን በታማኝነት በመክፈል በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ ዕዉቅና ተሰጠዉ።

የወላይታ ልማት ማህበር ባለፉት 2 ተከታታይ ዓመታት ማለትም በ2021ና 2022 እ.አ.አ በንግድ ዘረፍ በታማኝ ግብር ከፋይነት ከፌደራል ገቢዎች ሚንስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ የዕዉቅና ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል። ማህበሩ በተከታታይ ለ3ኛ ዙር በ2023 ላሳየዉም የላቀ አፈጻጸም በዛሬዉ ዕለት የዕዉቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል። ልማት ማህበሩ በሥሩ ያሉ የገቢ ማስገኛ ተቋማትን ሥር ነቀል ማሻሻያ በማድረግ በተከታታይ ትርፋማ እንዲሆኑ በማስቻል ለመንግሥት

ማህበሩ ግብርን በታማኝነት በመክፈል በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ ዕዉቅና ተሰጠዉ። Read More »

የወላይታ ልማት ማህበርና አርባምንጭ ተሃድሶ ማዕከል በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከተለያዩ ሀገር በቀልና አለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር የልማት ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ማህበሩ በትኩረት ይዞ ከሚሰራቸው የልማት ተግባራት አንዱ በሆነው የተቀናጀ ጤና በመሰረተ ማህረሰብ ተሃድሶ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የልማት ተግባራትን እያከናወነ ቆይቷል፤ እያከናወነም ነው፡፡ማህበሩ በዛሬው ዕለት ከአርባምንጭ ተሃድሶ ማዕከል ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት

የወላይታ ልማት ማህበርና አርባምንጭ ተሃድሶ ማዕከል በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡ Read More »