የወላይታ ልማት ማህበር ባለፉት 2 ተከታታይ ዓመታት ማለትም በ2021ና 2022 እ.አ.አ በንግድ ዘረፍ በታማኝ ግብር ከፋይነት ከፌደራል ገቢዎች ሚንስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፍ የዕዉቅና ሽልማት እንደተበረከተለት ይታወሳል። ማህበሩ በተከታታይ ለ3ኛ ዙር በ2023 ላሳየዉም የላቀ አፈጻጸም በዛሬዉ ዕለት የዕዉቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።
ልማት ማህበሩ በሥሩ ያሉ የገቢ ማስገኛ ተቋማትን ሥር ነቀል ማሻሻያ በማድረግ በተከታታይ ትርፋማ እንዲሆኑ በማስቻል ለመንግሥት በታማኝነትና በወቅቱ ግብር በመክፈል ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል።