ወላይታ ልማት ማህበር በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በመሬት መንሸራተትና በጎርፍ አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የ4 መቶ ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀኪሜ አየለ ወላይታ ልማት ማህበር በችግር ወቅት በአካል ተገኝቶ ላሳየዉ ወንድማዊ አጋርነትና ላደረገዉ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም ላቀረበዉ ማጽናኛ በራሳቸዉና በዞኑ ሕዝብ ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፉን የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበባየሁ ቶራ ከምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ እና የወላይታ ዞንና ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በጋራ በመሆን ለጋሞ ዞን አመራሮች አስረክበዋል።


ወላይታ ልማት ማህበር በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰብ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላዉ የጋሞ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።


