የማህበሩ ሰራተኞች በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡
ወላይታ ልማት ማህበር በአገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት የሚካሄደውን ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በማህበሩ የኮካቴ እንስሳት እርባታ ማዕከል ቅጥር ግቢ አካሂደዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና ጨምሮ የማህበሩ ሰራተኞች፣ የኢፈዴሪ የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ደቡብ ሪጅንና ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት
ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም የወላይታ ቴሌቪዥንና ወላይታ ዎጌታ ኤፍ 96.6 ሬዲዮ ጣቢያ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
ማህበሩ በመደበኛ የልማት ስራ የአፈርና አካባቢ ጥበቃ ስራ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያካሂድ ሲሆን በዚህም መልካም አፈጻጸም አለው፡፡











