ወላይታ ልማት ማህበር በዞኑ ውስጥ የተለያዩ የልማት ተግባራትን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ መንግስት የያዛቸውን የልማት ግቦች በትብብር ለማሳካት የራሱን ድርሻ እያበረከተ ቆይቷል፤ እያበረከተም ነው፡፡
ማህበሩ መንግስት በትምርትና ስልጠና ያየዘውንና የሰለጠና፣ ሀገር የሚያቀናና ስራ ፈጣሪ ዜጋ ለማፍራት የያዘውን ትልም ለማሳካት በራሱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚያደርገው ጥረት በዛሬው ዕለት ET- LEARNS ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያገኘውን በድጋፍ ያገኘውን ኮምፒውተርና ሰርቨር በዞኑ ለሚገኙ አስር ትምህርት ቤቶች በድጋፍ አበርክቷል፡፡
በድጋፍ ርክብክቡ ስፍራ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳንኤል ደሌ ማህበሩ መንግስት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ብሎም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት በማድነቅ ድጋፉ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ሀብቱን በአግባቡ በመጠቀም ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲያውሉ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና በበኩላቸው፤ ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከዚህም በፊት መሰል ተግባራትን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደቆየ በማስታወስ በዛሬው ዕለትም በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ 10 ትምህርት ቤቶች ለእያንዳንዳቸው 31 ክሮም ቡክ ኮምፒውተሮችና 1 ሰርቨር በድጋፍ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ ድጋፉ ዲጂታል ላይብራሪ ለማደራጀትና ለማጠናከር እንደሚረዳ፣ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት፣ ET- LEARNS ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት መገኘቱንም ጨምረው ተናግረው ድጋፉን ለማግኘት በተደረገው ርብርብ የተሳተፉ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወላይታ ዞን ደረጃ የሚገኙ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል፡፡
በድጋፍ አሰጣጡ መርሀ ግብር ለትምህርት ቤቶቹ የአይ.ተ መምህራን ስለኮምፒውተሮች አጠቃቀም ገለጻተደርጓል፡፡
በድጋፍ ርክብክቡ ስፍራ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ደንኤል ደሌ፣ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚካኤል ሳኦል እና ሌሎች የዞኑና የወረዳዎች የመንግሰት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
Wolaytta Worqaa Mayzzana!










