የዳግም ትምህርት ዕድል ፕሮጀክት ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር ከሉሚኖስ ፈንድ (Luminos Fund) በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች በ2017 የትምህርት ዘመን የሚተገብረውን የዳግም ትምህርት ዕድል (Second Chance Education) ፕሮጀክት የወረዳዎቹ ትምህርት አመራሮች በተገኙበት አስተዋወውቋል፡፡ ማህበሩ ፕሮጀክቱን በ2017 የትምህርት ዘመን በዳሞት ጋሌ፣ ቦሎሶ ሶሬ እና ባይራ ኮይሻ ወረዳዎች ይተገብራል፡፡

በዛሬው ዕለት ከወረዳዎቹ ለተወጣጡ የትምህርት አመራሮች ስለፕሮጀክቱ አተገባበር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ በሆኑት በወ/ሮ ብዙነሽ ሳሙኤል ማብራሪያና ገለጻ ተደርጓል፡፡

በፕሮጀክቱ ማስተዋወቂያ መድረክ የተገኙት የማህበሩ ዕቅድ ዝግጅትና ፕሮግራም ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ሌንጫ የወረዳዎቹ ትምህርት አመራሮች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ሁሉ ከፕሮጀከቱ ተግባራት አንዱ የሆነውን የተፋጠነ ትምህርት መርኃ ግብርን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አደራ ብለዋል፡፡

የዳግም ትምህርት ዕድል (Second Chance Education) ፕሮጀክት ዕድሜያቸው ለትምህርት ደርሶ በተለያየ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ልጆችን በተፋጠነ ትምህርት መርኃ ግበር ሙሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት በአንድ ዓመት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል በማስተማር ወደ 4ኛ ክፍል በማዛወር ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር እኩል በማድረግ ይሰራል፡፡ ፕሮጀክቱ ላለፉት አራት ዓመታት በዞኑ ባሉት በተለያዩ ወረዳዎች ከ2600 በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *