ማህበሩ ለወጣቶች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የጸጉር ማስተካከያ ዕቃዎችን ገዝቶ አበረከተ፡፡

ማህበሩ ለወጣቶች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የጸጉር ማስተካከያ ዕቃዎችን ገዝቶ አበረከተ፡፡

የወላይታ ልማት ማህበር በሁለንተናዊ ልማት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያየ ጊዜ በሚተገብራቸው የልማት ተግባራት ተጠቃሚ አድርጓቸዋል፡፡ ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለወጣቶች የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና በመስጠትና በማህበር ተደራጀተው በቁጠባ በመሰማራት ኑሮአቸውን እንድያሻሽሉ ሁኔታዎችን በመማመቻቸት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

ልማት ማህበሩ ከጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ላለፉት ሶስት ዓመታት እየተገበረ በቆየው WORK (Wider Opportunities, Resource and Knowledge) ፕሮጀክት በድጉና ፋንጎ ወረዳና በበሌና ገሱባ ከተማ አስተዳደሮች በኢንተርፕራይዝ ማህበር አደራጅቶ በጸጉር ማስተካከል ሙያ ላሰለጠናቸው አስር ማህበራት ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ሙሉ የወንዶችና የሴቶች ጸጉር ማስተካከያ ቁሳቁስ በመግዛት አበርክቷል፡፡ በቁሳቁስ ርክብክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና የማህበሩ አባላት በተሰጣቸው ቁሳቁስ ጠንክረው በመስራት ራሳቸውን ለመለወጥ እንዲሰሩ መልዕክት አስላተልፈዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለሆኑና በጸጉር ማስተካከል ሙያ ለሰለጠኑ 10 የኢንተርፕራይዝ ማህበራት እንደየፍላጎቶቻቸው ለሁለት ማህበራት የወንዶች ጸጉር እና ለስምንቱ ደግሞ የሴቶች ጸጉር ማስተካከያ ቁሳቁስ ተገዝቶ መበርከቱን በወላይታ ልማት ማህበር የ WORK (Wider Opportunities, Resource and Knowledge) አስተባባሪ አቶ ግዘቸው ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በቀን 12/10/16 ዓ.ም በተደረገው የቁሳቁስ ርክብክብ ስነስርዓት የየወረዳዎች አስተዳዳሪዎች፣ የኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት ኃለፊዎች እንዲሁም የማህበራቱ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የመዋቅሮቹ የስራ ኃላፊዎች ለወጣቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

1 thought on “ማህበሩ ለወጣቶች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የጸጉር ማስተካከያ ዕቃዎችን ገዝቶ አበረከተ፡፡”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *