የወላይታ ልማት ማህበር የምሁራን መፍለቂያ የሆነዉን የወላይታ ሊቃ ት/ቤት ለማጠናከር ከመጋቢት ወር ጀምሮ እያካሄደ ባለዉ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከመላዉ ዓለም ሁሉም የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች መሳተፋቸው ይታወቃል ።
በዛሬው ዕለት ደግሞ በማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የልማት ማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በአቃቂ ክ/ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ እየተካሄደ ባለዉ ንቅናቄ የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዉ ለትምህርት ቤቱ ማጠናከሪያ ከዚህ በፊት ካደረጉት ድጋፍ ተጨማሪ ድጋፍ ለማሰባሰብ በክፍለ ከተማዉ ስራ አስፈፃሚዎች ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል። ንቅናቄው ቀጥሎ በተመሳሳይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚደረግ ይሆናል።
ወልማ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ለማጠናከር በጀመረዉ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የትምህርት ቤቱን ዙርያ አጥር ግንባታ እያጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ምዕራፍ ሌሎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን የሚያሟላ ይሆናል።
በንቅናቄዉ የወልማ ስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የወልማ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስራ አስፈጻሚ አባላትና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።