በአካትቶ ልማት ዘላቂነት ዙርያ ምክክር ተደረገ።
የወላይታ ልማት ማህበር ከCBM (Christian Blind Mission) ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ በቦሎሶ ቦምቤ፣ ኪንዶ ኮይሻና ዳሞት ሶሬ ወረዳዎች በሚተገበረው CBID(Community Based Inclusive Development) ፕሮጀከት አካል ጉዳተኞችንና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመደገፍና የማብቃት ስራ ይሰራል።
ፕሮጀክቱ ከሰሞኑ በሶስቱም ወረዳዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ ስላለው የአካትቶ ልማት ተግባራት ቀጣይነት ምክክር ተደርጓል።
በዳሞት ሶሬ ወረዳ ምክክር ላይ የተገኙት የወረዳዉ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ ዳና ወረዳዎች አከትቶ ልማት ላይ ከበጀት ጀምሮ አቅደዉ መስራት አለባቸዉ ብለዋል።
በወላይታ ልማት ማህበር የCBID ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አዲስዓለም አሰፋ በረጂ ድርጅቱ ድጋፍ እየተተገበረ ያለዉ ይህ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዉ ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላም ቢሆን ተግባራቱ ተጠናክረዉ መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።
ከተለያዩ ባለድርሻ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመጡ የምክክሩ ተሳታፊዎችም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ልማት ማህበሩ እየተገበራቸዉ ያሉ ስራዎችን እርስ በርስ በመቀናጀት እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል።
የወላይታ ልማት ማህበር የአካትቶ ልማት እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ፕሮጀክቶችን በዞኑ አምስት ወረዳዎች እየተገበረ ያለ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃሉ።