ወላይታ ልማት ማህበር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ የያዘውን ዕቅድ ዕውን ለማድረግ ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ይገኛል ።

‎የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የልማት ማህበሩ የበላይ ጠባቂ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በንግግራቸው የተደረገው ድጋፍ ተማሪዎቻችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በእውቀት በመደገፍ የውጤት ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ የማድረግ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ናና ማህበሩ በትምህርት ዘርፍ ለሚሰራቸው ሥራዎች መሳካት የግብረሰናይ ድርጅቶች፣ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ያላቸው ሚና የማይዘነጋ መሆኑን ገልፀዋል ።

አቶ ሱሌይማን ዳዊት የሳቫና ፕሪንትንግ ፕሬስ መሥራች እና ባለቤት የወላይታ ህዝብ የመማር እና የመለወጥ ፍላጎቱን መገንዘባችን ነው አብረን እንድንሰራ ያነሳሳን በማለት በቀጣይም አብሮነታቸው እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።