ወላይታ ልማት ማህበር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡
ማህበሩ በትብብር ከሚሰራቸው ተቋማት አንዱ የሆነውና ከዚህ በፊት ከማህበሩ ጋር በመሆን በዞኑ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርትን ለማስፋፋት የራሱን ድርሻ እያበበረከተ የቆየ ET-LEARNS የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ኮምፒውተሮችና ሰርቨር ለልማት ማህበሩ አበርክቷል፡፡ ድጋፉ 310 ክሮም ቡክ ኮምፒውተሮችንና 10 ሰርቨሮችን እንዲሁም የኮምፒውተሮቹ ሙሉ አክሴሰሪዎች ያካተተ ነው፡፡
የተበረከቱ ኮምፒውተሮችና ሰርቨሮች ማህበሩ በዞኑ ውስጥ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለያዘው ዕቅድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፡፡
ማህበሩ በዚሁ በተገኘው የኮምፒውተርና ሰርቨር ድጋፍ በወላይታ ዞን በተመረጡ አስር ትምህርት ቤቶች የዲጂታል ላይብራሪ በማደራጀት ተማሪዎች ከትምህርት ነክ ድረገጾች በቂ የማጣቀሻ መጽሐፍትን በማግኘት አንብበው በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል አልሞ ነው፡፡
ወላይታ ልማት ማህበር ከድርጅቱ ጋር በመተባበር በመሰል ስራ በወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ዲጂታል ላይብራሪ በማደራጀት የትምህርት ቤቱን ተማሪዎች ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል፡፡





