በወላይታ ልማት የጠበላ ከተማ ቅርንጫፍ አባላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት ተካሂዷል ።
በጉባኤው የከተማዉ የልማት ማህበሩ አባላት የተገኙ ሲሆን የማህበሩና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2024 እ.አ.አ ክንዉን ሪፖርትና የ2025 ዕቅድ በዝርዝር ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዉ ጸድቀዋል።
ጉባኤዉን በንግግር የከፈቱት የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እጩ ዶ/ር ታረቀኝ ገቼረ ማህበሩ በአሁን ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ ይሻል በማለት ማህበሩን ማጠናከር የሁሉም አባል ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።
የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና በበኩላቸው የማህበሩ ዋነኛው የሀብት ምንጭ አባላቱ ስለሆኑ በልማት ማህበሩ እንቅስቃሴ ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡ ጨምረውም በዚህ ከአባላት በሚገኝ ሀብት በዞኑ ብሎም በጠበላ ከተማ አስተዳደር የሚሰራቸውን የልማት ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎችም አስተያየት ሲሰጡ ማህበሩ በዞኑ ልማት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው አጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል፡፡
በጉባኤው መጨረሻ በ2024 እ.አ.አ ሀብት አሰባሰብ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የዕውቅና ምስክሮ ወረቀት ተበርክቷል፡፡








