የወላይታ ሊቃ ተማሪ የነበሩ አርባ ሶስት ሐኪሞች መመረቃቸዉ ተገለጸ !!
September 26,2022 ከዛሬ ሰባት አመት በፊት ወላይታ ሊቃ ተማሪ የነበሩ ሴት 08 ወንድ 35 በድምሩ 43 (አርባ ሶስት) ዶክተሮች ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸዉን
አጠናቅቀዉ መመረቃቸዉን ወላይታ ልማት ማህበር ገለጸ፡፡ የወላይታ ሊቃ ት/ቤት በ2013ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዉጤትም በአገር ደረጃ አንደኛ መሆኑ ና ሊቃ ት/ቤት
ከተመሰረተ እስ ከ አሁን ድረስ ዉጤታማ የመሆኑ ሚስጥር ወላይታ ልማት ማህበር ፤ የትምህርት ቤቱ አስተዳደርና በተለይም መምህራን፤ በተማሪዎቹ ብርቱ ጥረት እንዲሁም የተለያዩ
ባለድርሻ አካላት በሚያደርጉት ብርቱ ክትትልና ድጋፍ እንደሆነ የዛሬዎቹ ተመራቂዎቹ ማሳያ ናቸዉ፡፡ ይህንን የተማሪዎች ምረቃ ምክንያት በማድረግ ወላይታ ልማት ማህበር ከሐዋሳ
ወልማ ቅ/ጽ/ቤት ጋር በጋራ ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ባዘጋጀዉ event የቀድሞ የወላይታ ሊቃ ተማሪዎች አለሙናይ፤ ተመራቂ ተማሪዎች፤ የወልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል ::
በዛሬው ዕለት የወላይታ ሊቀ ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑ 31 የህክምና ዶክተሮች ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡
ወላይታ ልማት ማህበር ከድህነትና ኋላ ቀሪነት የተላቀቀ ወላይታን የማዬት ራዕዩን እውን ለማድረግ ትምህርት ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን በማመን በኢትዮጵያ ሚሊኒዬም ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን አቋቋመ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በስኬት ጎዳና በመጓዝ ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፍራት አካባቢውን በበጎ ጎን ስሙ ከፍ እንዲል የራሱን ሚና ሲጫወት ቆይቷል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ዓመታት በሀገርአቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት በመሪነትና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እንዳሳለፈ የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ከስምንት መቶ ሃምሳ በላይ ተማሪዎችን ወደ የኒቨርሲቲ አስገብቷል፡፡
በአጠቃላይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ተማሪዎች ከ300 በላይ የሚሆኑት በሜዲካል ዶክትሬት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የተቀላቀሉ ሲሆን አብዛኞቹ ተመርቀው በሙያቸው ሀገራቸውን እያገለገሉ ናቸው፤ ሌሎቹ የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው፡፡
ትምህርት ቤቱ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፍራት እስካሁን በአሜሪካ፣ አውሮጳና ኤዢያ በሚገኙ እውቅ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው በተለያየ ሙያ የተሰማሩ እና ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉ ከ100 በላይ ተማሪዎች እንዳሉት ይተወቃል፡፡ ማህበሩ የትምህርት ቤቱን ተደራሽነት ለማስፋፋት በዞኑ በቦዲቲ፣ አረካና ገሱባ ከተማ አስተዳደሮች በማቋቋም ለማህበረሰቡ ጥያቄ በቂ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የትምህርት ቤቱ ፍሬዎች የሆኑ ተማሪዎች በየዓመቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ሲሆን ዘንድሮ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ብቻ 31 ሜዲካል ዶክተሮች በአንድ ላይ በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡ ከዚህ በፊት ከዚሁ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ህክምና ትምህርት ኮሌጅ (ጥቁር አንበሳ ) በርካታ ቁጥር ያላቸው የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ መመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
ወላይት ልማት ማህበር ተመራቂ ተማሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን እንኳን ለዚህ ጣፋጭ ድል በሰላም አደረሳችሁ እያለ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡ ተመራቂዎች በተመረቁበት የተከበረ ሙያ ለህዝቡ በገቡት ቃለ መሐላ መሰረት ተገቢ አገልግሎትን በታማኝነት በመስጠት ከማህራችንና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ድህነትንና ኋላ ቀሪነትን ለመቀነስ በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በድጋሚም ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!