የወላይታ ልማት ማህበር ማኔጅመንት አባላት ከወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ለመተግበር በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡
ወላይታ ልማት ማህበር መንግስት ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ በማልማት የራሱን ድርሻ ሲወጣ እንደቆየ ይታወቃል፡፡
ማህበሩ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በመሳተፍ የማኔጅመንት አባለቱንና የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት አመራሮችን፣ መምህራንና ተማሪዎችን በማስተባበር በግቢው የተለያዩ የዛፍ ችግኝ ዓይነቶችን አስተክሏል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና ትምህርት ቤቱ በዘንድሮ የክልል አቀፍ 8ኛ ክፍል ፈተና ላዝመዘገበው የላቀ ውጤት መላውን የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ በማመስገን የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና በደቡብ ክልልና በወላይታ ዞን ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ይታወቃል፡፡





