Construction Section
The Construction Company has GC-4 license in Construction & offers quality services for Wolaitta Zone & the Surrounding in Construction of buildings, ditches, culverts, pebble roads & bridges, spring Capping etc.…
Projects Under Construction by Damotta Construction Company
No | Project Name | Project Site |
---|---|---|
1 | WODA Head Office Building (Wolaitta Community Development Building) | Soddo Town |
2 | Industrial Engineering Center | Soddo Town |
3 | Garage | Soddo Town |
4 | Kokate Marachare Dairy | Soddo Town |
5 | Bitena Town Youth Training & Dodgem Center | Duguna Fango |
6 | Areka Town Ditch | Areka Town |
7 | Mure High School 2 Blocks Building | Offa |
8 | Dangara Salata High School Building | Boloso Sore |
9 | Boditti Town Walacha river Bridges | Boditti Town |
10 | Firew Altaye Monument Building | Soddo Town |
11 | Beklo Segno Spring water extension project | Bayra Koysha |
Total Running Projects Under Damotta Construction | 11 |
የኩባንያው የግንባታ ስራዎች አፈጻጸም በከፍተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ለወላይታ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ገንብቶ ያጠናቀቀውን ቢሮ ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡
በወላይታ ልማት ማህበር የሚተዳደረው የዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ጥራት ያላቸውን ግንባታዎች በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት ገንብቶ እንደሚያጠናቅቅ ይታወቃል፡፡ ኩባንያው ከግንባታ ስራዎች በተጨማሪ ማሽኔሪዎችን በማከራየትና ሲሚንቶ በማከፋፈል ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ኩባንያው በዛሬው ዕለት ለወላይታ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ገንብቶ ያጠናቀቀውን የቢሮ ህንጻ የወላይታ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክቧል፡፡ በርክብክቡ ስነስርዓት የተገኙት የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል የኩባንያው የግንባታዎች አፈጻጸም አቅም በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በመናገር ይህ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የመምሪያውን ህንጻ በዞኑ በተለያዩ ሴክተሮች ያለውን የቢሮ ችግር እንደሚያቃልል ተናግረዋል፡፡
የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና በበኩላቸው ከማህበሩ የገቢ ማስገኛ ተቋማት አንዱ የሆነው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ የሚሰራቸውን የግንባታ ስራዎች በፍጥነትና በከፍተኛ ጥራት እያከናወነ እንደሆነ ገልጸው የዞኑ አስተዳደር ሂደቱን በመከታተል በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ላደረገው ትብብር አመስግነዋል፡፡
የወላይታ ዞን ሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ መመሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ኩማ ይህ አዲሱ ህንጻ ከዚህ በፊት በመምሪያው የነበረውን የቢሮ ጥበትና ምቹ ያልሆነ የስራ አካባቢ ችግርን እንደሚያቃልል ተናግረዋል፡፡