News

WODA News

በመትከል ማንሰራራት

የማህበሩ ሰራተኞች በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ አኖሩ፡፡ ወላይታ ልማት ማህበር በአገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት የሚካሄደውን ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በማህበሩ የኮካቴ እንስሳት እርባታ ማዕከል ቅጥር ግቢ አካሂደዋል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ናና […]

በመትከል ማንሰራራት Read More »

ማህበሩ ከየትኛዉም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ ተነገረ።

በወላይታ ልማት የጠበላ ከተማ ቅርንጫፍ አባላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት ተካሂዷል ።በጉባኤው የከተማዉ የልማት ማህበሩ አባላት የተገኙ ሲሆን የማህበሩና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2024 እ.አ.አ ክንዉን ሪፖርትና የ2025 ዕቅድ በዝርዝር ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዉ ጸድቀዋል።ጉባኤዉን በንግግር የከፈቱት የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እጩ ዶ/ር ታረቀኝ ገቼረ ማህበሩ በአሁን ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ ይሻል በማለት ማህበሩን ማጠናከር

ማህበሩ ከየትኛዉም ጊዜ ይልቅ የአባላት ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ ተነገረ። Read More »

ከጎዳና ለተመለሱ ልጆች ወላጆች የንግድ ስራ መነሻ ካፒታልና ንብረት ተሰጣቸው፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር አሜሪካን ሀገር ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማና አካባቢው ከሚገኙ የወላይታ ተወላጆች ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በመምጣት ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትን ወደቤተሰቦቻቸው በመመለስ ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ እነዚህን ህጻናት በማቋቋምና በዘላቂነት የልጆቹን ቤተሰብ ኑሮ ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ የሚታወስ ሲሆን ለልጆቹ የትምርት ቁሳቁስ፣ ቀለብ፣ የጤና መድህን ሽፋንና ሌሎች

ከጎዳና ለተመለሱ ልጆች ወላጆች የንግድ ስራ መነሻ ካፒታልና ንብረት ተሰጣቸው፡፡ Read More »

ማህበሩ ለ10 ትምህርት ቤቶች 310 ኮምፒውተሮችንና 10 ሰርቨሮችን አበረከተ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በዞኑ ውስጥ የተለያዩ የልማት ተግባራትን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ መንግስት የያዛቸውን የልማት ግቦች በትብብር ለማሳካት የራሱን ድርሻ እያበረከተ ቆይቷል፤ እያበረከተም ነው፡፡ ማህበሩ መንግስት በትምርትና ስልጠና ያየዘውንና የሰለጠና፣ ሀገር የሚያቀናና ስራ ፈጣሪ ዜጋ ለማፍራት የያዘውን ትልም ለማሳካት በራሱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚያደርገው ጥረት በዛሬው ዕለት ET- LEARNS ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያገኘውን

ማህበሩ ለ10 ትምህርት ቤቶች 310 ኮምፒውተሮችንና 10 ሰርቨሮችን አበረከተ፡፡ Read More »

ማህበሩ ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ 8 የመማሪያ ክፍሎች የያዘ 2 ብሎክ ህንጻ አስመረቀ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት የትኩረት አቅጣጫ ዘርፍ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ከመንግስት ጎን በመሆን ለትምህርት ተደራሽነትና ጥራት መረጋገጥ የራሱን ሚና ተወጥቷል፤ እየተወጣም ነው፡፡ ማህበሩ ከዚህ በፊት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የመማሪያ ህንጻዎችን በመገንባት ለመንግስት ያስረከበ ሲሆን በዘሬው ዕለት በኦፋ ወረዳ ሙሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለት ብሎክ 8 የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ህንጻ ገንብቶ በማጠናቀቅ

ማህበሩ ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ 8 የመማሪያ ክፍሎች የያዘ 2 ብሎክ ህንጻ አስመረቀ፡፡ Read More »

ማህበሩ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮምፒውተርና ሰርቨር ድጋፍ አገኘ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በትብብር ከሚሰራቸው ተቋማት አንዱ የሆነውና ከዚህ በፊት ከማህበሩ ጋር በመሆን በዞኑ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርትን ለማስፋፋት የራሱን ድርሻ እያበበረከተ የቆየ ET-LEARNS የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ኮምፒውተሮችና ሰርቨር ለልማት ማህበሩ አበርክቷል፡፡ ድጋፉ 310 ክሮም ቡክ

ማህበሩ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮምፒውተርና ሰርቨር ድጋፍ አገኘ፡፡ Read More »

ማህበሩ ከGIZ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገለት፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በዘላቂነት የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በያዘው ዕቀድ በዞኑ ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና አስተራረስ እንዲለማመዱ ከተለያዩ ግብረሰናይ ደርጅቶች ጋር በመተባበር ይሰራል፡፡ ማህበሩ የመስኖ እርሻንና የንብ ማነብ ስራን ለማዘመን፣ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ወዘተ… ስራዎችን በመስራት አያለ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንዳደረገና እያደረገ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ልማት ማህበሩ በዚሁ ዘርፍ በሚያደርገው ርብርብ GIZ የተሰኘ የጀርመን

ማህበሩ ከGIZ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገለት፡፡ Read More »

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ወላይታ ሊቃ ትምሀርት ቤትን ጎበኙ።

በተለያዩ አካባቢዎች የልማት ስራዎችን እየጎበኘ ያለዉና በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ ልዑካን ቡድን በወላይታ ሶዶ ከተማ ተገኝተዉ የተሞክሮ ማዕከል የሆነዉን ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ጎብኝቷል። ልዑካን ቡድኑ በትምህርት ቤቱ ያለዉን የመማር ማስተማርና ሌሎች ተግባራትን በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ናና ማብራሪያ ተሰጥቶታል ። ዶ/ር መቅደስ በጉብኝቱ የትምህርት ቤቱን ተማሪዎች በክፍሎች፣

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ወላይታ ሊቃ ትምሀርት ቤትን ጎበኙ። Read More »

በዛሬው ዕለት የወላይታ ሊቀ ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑ 31 የህክምና ዶክተሮች ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር ከድህነትና ኋላ ቀሪነት የተላቀቀ ወላይታን የማዬት ራዕዩን እውን ለማድረግ ትምህርት ወሳኝ መሳሪያ መሆኑን በማመን በኢትዮጵያ ሚሊኒዬም ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን አቋቋመ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በስኬት ጎዳና በመጓዝ ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፍራት አካባቢውን በበጎ ጎን ስሙ ከፍ እንዲል የራሱን ሚና ሲጫወት ቆይቷል፡፡ ትምህርት ቤቱ ከ2005 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የወላይታ ሊቀ ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑ 31 የህክምና ዶክተሮች ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡ Read More »

ማህበሩ በወላይታ ሊቃ ት/ቤት ባለአንድ ብሎክ የመማሪያ ህንጻ ግንባታ አስጀመረ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር በሀገር አንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስመጥር እና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን በማፋራት የሚታወቀውን ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ለማጠናከርና ለማስፋፋት በያዘው ዕቅድ ባሳለፍነው ዓመት የሀብት ማሰባበሰቢያ መርሀ ግብር በመንደፍ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ ሀብት ማሰባበሰቡ ይተወቃል፡፡ ለትምህርት ቤቱ ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ድጋፍ ለማድረግ በወቅቱ ቃል ከገቡ ባለሀብቶች መካከል ሀጂ ሙስጠፋ አወል (የሙለጌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለቤት) እና ቤተሰቡ አንዱ

ማህበሩ በወላይታ ሊቃ ት/ቤት ባለአንድ ብሎክ የመማሪያ ህንጻ ግንባታ አስጀመረ፡፡ Read More »