ጠቅላላ ጉባኤው የወላይታ ልማት ማህበርን የሚመሩ ቦርድ አመራሮች ምርጫ በማካሄድ ተጠናቅቋል።
ጠቅላላ ጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ የመረጠ ሲሆን ሰብሳቢውም ለጉባኤው የሥራ መመሪያ አስተላልፈዋል።
የልማት ማህበሩን የሚመሩ የአመራር ቦርድ አባላት:-
1. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገ/መስቀል ጫላ የወላይታ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ
2. በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ የወላይታ ልማት ማህበር የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ
3. የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ጤራ የማህበሩ አባል
4. በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ የማህበሩ አባል
5. የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል የማህበሩ አባል
6. የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል አባል
7. ዶ/ር ብርሃነፀሐይ ገ/መስቀል የማህበሩ አባል
8. የወላይታ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋ ፋንታ የማህበሩ አባል
9. አቶ ጥላሁን ፋንታ የማህበሩ አባል
10. አቶ ፈለቀ ፋንታ የማህበሩ አባል
11. የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አበሻ ሽርኮ የማህበሩ አባል
የጠቅላላ ጉባኤው ኮሚቴ
1. ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ
2. አቶ መንግሥቱ ትግሮ
3. ዶ/ር ማርቆስ ጩምቡሮ
የበጀትና የቁጥጥር ኮሚቴ
1. ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ የበጀትና ቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ
2. አቶ ዘካሪያስ ታደሰ የበጀትና ቁጥጥር ኮሚቴ ም/ ሰብሳቢ
3. ዶ/ር ፋኖስ ዛና አባል