ወላይታ ልማት ማህበር በድህነትና በሌሎች ገፊ ምክንያቶች ወደ ጎዳና የወጡ ልጆችን ከጎዳና ላይ በማንሳት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲቀላቀሉ በማድረግና የቤተሰቦቻቸው ኑሮ በዘላቂነት እንዲሻሻል ከአጋሮች ጋር በመሆን እየሰራ ነው፡፡
ማህበሩ በአገረ አሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማና አካባቢው ከሚገኙ የወላይታ ዳያስፖራ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሚተገብረው በዚሁ REST (Reintegration and Empowerment of Street Children) ፕሮጀክት ባሳለፍነው ዓመት ልጆችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የስነ ልቦና ስልጠና በመስጠት እንዲሁም ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ አሟልቶ ባሉበት የክፍል ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግና የቀለብ ድጋፍ በመስጠት የቆየ ሲሆን ለዘንድሮ የትምህርት ዘመንም አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አስችሏል፡፡
ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ልጆች በዛሬው ዕለት የአልባሳትና ጫማ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከዚህ በፊትም የልጆቹ ቤተሰቦች በዘላቂነት ኑሮአቸውን እንዲያሻሽሉ የዶሮ ድጋፍ፣ የዓመት በዓል መዋያና ቀለብ ድጋፍ ተደርጎላቿል፡፡ በተጨማሪም በቤተሰብ ደረጃ የጤና መድህን ክፍያ ከአምና ጀምሮ እየተከፈላቸው ይገኛል፡፡
REST (Reintegration and Empowerment of Street Children Project) ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ወላይታ ልማት ማህበር በአሜሪካ ሀገር ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር ከተማና አካባቢው ከሚገኙ ዳያስፖራ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሚተገብር የተቀናጀ ፕሮጀክት ነው፡፡